በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።
ዘፀአት 25:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መባ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፤ በፈቃዱ ሊሰጠኝ ልቡ ከተነሣሣ ሰው ሁሉ መባዬን ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስጦታን ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤላውያን ንገር፤ ማንኛውም ሰው በፈቃዱ የሚያመጣውን መባ ሁሉ ተቀበል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤልን ልጆች በልባችሁ ያሰባችሁትን ከገንዘባችሁ መባ አምጡልኝ” በላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስጦታ ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፤ በገዛ እጁ ሊሰጠኝ በልቡ ከሚያምረው ሰው ሁሉ መባ ተቀበሉ። |
በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።
ከአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶች፥ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤት በመጡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው እንዲሠራ በፈቃዳቸው መባ ሰጡ።
ከዚያም በኋላ ዘወትር የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የወር መባቻና፥ የተመረጡና የተቀደሱ የጌታ በዓላት ሁሉ መሥዋዕት፥ ሰውም ሁሉ ለጌታ በፈቃድ የሰጠውን ቁርባን አቀረቡ።
በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ በሙሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚሰጡትን ይዘህ ሂድ።
ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን የሚያቀርቡትን የእስራኤልን ልጆች አሥራት ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህ፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም አልኋቸው።”