መክብብ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሆነው ነገር በሙሉ ስሙ አስቀድሞ ተጠርቷል፥ ሰውም ማን እንደሆነ ታወቀ፥ ከእርሱ ከሚበረታው ጋር መፋረድ አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋራ፣ ማንም አይታገልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ነገር ሁሉ ስም ተሰጥቶታል፤ የሰዎችም ማንነት ታውቆአል፤ ከእነርሱ በላይ ብርቱ ከሆነው ጋር መቋቋም አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሆነው ሁሉ እነሆ፥ ስሙ አስቀድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፤ ከእርሱም ከሚበረታው ጋር ይፋረድ ዘንድ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሆነውም ስሙ አስቀድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፥ ከእርሱ ከሚበረታው ጋር ይፋረድ ዘንድ አይችልም። |
እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርረዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው?