ኤርምያስ 49:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርረዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 “አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ። የመረጥሁትን በርሱ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 አንበሳ ጥቅጥቅ ካለው ከዮርዳኖስ ጫካ ወጥቶ ለምለም ወደ ሆነው ወደ በጎች መሰማርያ መስክ እንደሚመጣ እኔም በድንገት መጥቼ የኤዶም መሪዎችን አባርራለሁ፤ ከዚህ በኋላ የምመርጠውን እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ሊጠይቀኝ የሚደፍር ማን ነው? በፊቴ ቆሞ የሚቋቋመኝስ መሪ ማን ነው? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እነሆ፥ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል፥ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፥ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው? Ver Capítulo |