ዘዳግም 33:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፥ በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፥ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ነው፤ በወንድሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ አሴር ነገድም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ነገዶች ሁሉ ይበልጥ የተባረከ ይሁን፤ እርሱም በወንድሞቹ ዘንድ የተወደደ ይሁን፤ ምድሩም በወይራ ዛፍ የበለጸገች ትሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ አሴር ከልጆች የተነሣ የተባረከ ይሁን፤ ለወንድሞቹም የተመረጠ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ያጥባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ 2 አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፤ 2 በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። |