Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 33:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ስለ አሴር ነገድም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ነገዶች ሁሉ ይበልጥ የተባረከ ይሁን፤ እርሱም በወንድሞቹ ዘንድ የተወደደ ይሁን፤ ምድሩም በወይራ ዛፍ የበለጸገች ትሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ነው፤ በወንድሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ “አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፥ በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፥ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ስለ አሴ​ርም እን​ዲህ አለ፦ አሴር ከል​ጆች የተ​ነሣ የተ​ባ​ረከ ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የተ​መ​ረጠ ይሁን፤ እግ​ሩ​ንም በዘ​ይት ያጥ​ባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦ 2 አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፤ 2 በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 33:24
11 Referencias Cruzadas  

“አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤ በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል።


እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር።


ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!


ሚስትህ በቤትህ እንደ ፍሬያማ የወይን ተክል ትሆናለች፤ ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ለምለም ቅርንጫፎች ይሆናሉ።


የልጆችህን ልጆች ለማየት እንድትበቃ ያድርግህ! ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!


እስከሚነጋም ድረስ ከሥጋው ምንም ነገር አታስተርፉ፤ የተረፈ ነገር ቢኖር ሁሉንም በእሳት አቃጥሉት።


ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው። ንጉሡም በግብጽና በቤቱም ሁሉ ላይ አዛዥ አደረገው።


በዚህ ሁኔታ ክርስቶስን የሚያገለግል ሰው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።


የምትጸልዩልኝም በይሁዳ ምድር ካሉት ከማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለኝ አገልግሎትም በእግዚአብሔር ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው።


ስለዚህ እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞች ለአሴር ነገድ በየወገኖቻቸው ርስት ሆነው የተሰጡ ድርሻዎች ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos