ዘዳግም 24:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቈጠርልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለብሶት ያድር ዘንድ ፀሐይ ሳትጠልቅ መልስለት፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለብሶት እንዲተኛ እንዲባርክህም ፀሐይ ሳይገባ መያዣውን ፈጽመህ መልስለት፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ምጽዋት ይሆንልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብሶት እንዲተኛ እንዲባርክህም ፀሐይ ሳይገባ መያዣውን ፈጽመህ መልስለት፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅ ይሆንልሃል። |
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”