ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ዘዳግም 23:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእግዚአብሔር ለጌታ ስእለት በተሳልህ ጊዜ እግዚአብሔር ጌታ ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና ከመክፈል አታዘገይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት ከተሳልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር አጥብቆ ከአንተ ይሻዋልና፣ ኀጢአት እንዳይሆንብህ ለመክፈል አትዘግይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእግዚአብሔር አምላክህ ስእለት በምታደርግበት ጊዜ ለመስጠት ወይም ለመፈጸም ቃል የገባህበትን ስእለት አታዘግይ፤ እግዚአብሔር አንተ የገባኸውን ቃል እንድትፈጽም ይፈልጋል፤ ስእለትህን ካልፈጸምክ ግን ኃጢአት ይሆንብሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኀጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘግይ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘገይ። |
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።
ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።