Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከአንተ ጋር ላለው ለአንዱ ድሃ ወገኔ ገንዘብ ብታበድረው፥ እንደ ባለ አራጣ አትሁንበት፥ ወለድም አታስከፍለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በእናንተም ላይ ተቈጥቼ በጦርነት እንድታልቁ አደርጋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ ባል አልባ፥ ልጆቻችሁም አባት አልባ ሆነው ይቀራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ቍጣ​ዬም ይጸ​ና​ባ​ች​ኋል፤ በሰ​ይ​ፍም አስ​ገ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም መበ​ለ​ቶች፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ድሀ-አደ​ጎች ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ቍጣዬም ይጸናባችኋል፥ በሰይፍም አስገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁም መበለት፥ ልጆቻችሁም ድሀ አደጎች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:24
21 Referencias Cruzadas  

በልቤም አሰብሁና መኳንንቶቹንና ሹማምቱን ተከራከርኋቸው፥ እንዲህም አልኋቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁ በአራጣ ታበድራላችሁ”፤ ትልቅ ጉባኤም ሰበሰብሁባቸው።


የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም።”


የክፉና የተንኰለኛ አፎች በላዬ ተላቅቀውብኛልና፥ በሐሰት አንደበትም በላዬ ተናገሩ፥


ልጆቹም ያለ አባት ይቅሩ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።


ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።


ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ወገባቸውም ዘወትር ይንቀጥቀጥ።


የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።


የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?


መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።


ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጉልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።


ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፥ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል።


“ወንድምህ ቢደኸይ፥ እርሱም በአንተ ዘንድ ራሱን መቻል ቢያቅተው፥ አጽናው፤ እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛም ከአንተ ጋር ይኑር።


ወንድምህ ከአንተ ጋር እንዲኖር ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።


በቁጣው ፊት ማን ይቆማል? የቁጣውንስ ንዳድ ማን ይቋቋማል? መዓቱ እንደ እሳት ፈሰሰ፤ ከእርሱ የተነሣ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ።


ስጡ ይሰጣችኋልም፤ በመልካምም መስፈሪያ የተጠቀጠቀና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና።”


ለእንግዳው በወለድ አበድረው፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ ለወንድምህ በወለድ አታበድር።


ለእግዚአብሔር ለጌታ ስእለት በተሳልህ ጊዜ እግዚአብሔር ጌታ ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና ከመክፈል አታዘገይ።


በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos