ዘዳግም 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፥ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፥ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ባርኳችኋል፤ በዚህ ጭልጥ ባለው ምድረ በዳ ባደረጋችሁት ጕዞ ጠብቋችኋል። በእነዚህ አርባ ዓመታት አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ነበርና አንዳችም ነገር አላጣችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም። |
እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፥ አገነነውም፥ በጎችንና ላሞችን፥ ብርንም፥ ወርቅንም፥ ወንዶች ባርያዎችንና ሴቶች ባርያዎችን፥ ግመሎችንም፥ አህዮችንም ሰጠው።
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ የግብፃዊውን ቤት ባረከ፥ የጌታም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
“ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ።
ጌታም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ እያንዳንዱም ቀን እንደ አንድ ዓመት ሆኖ፥ በደላችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ መከፋቴንም ታውቃላችሁ።’
“ከኮሬብም ወጣን፥ ጌታ አምላካችን እንዳዘዘን በታላቁ እጅግም በሚያስፈራ በዚያ ሁሉ ባያችሁት ምድረ በዳ በኩል በተራራማው በአሞራውያን መንገድ ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።
የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።
ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር።