የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።
አሞጽ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” ይላል ጌታ። “እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ እስራኤላውያን፣ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር “እስራኤልን ከግብጽ፣ ፍልስጥኤማውያንን ከቀፍቶር፣ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእኔ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ከእናንተ አያንሱም፤ እናንተን ከግብጽ እንዳወጣሁ እንደዚሁም ፍልስጥኤማውያንን ከቀርጤስ፥ ሶርያውያንን ከቂር አላወጣሁምን? አውጥቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከቀጰዶቅያ፥ ሶርያውያንንም ከጕድጓድ ያወጣሁ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? |
የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጉስቁልና ይነዳቸዋል።
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና።
የደማስቆንም መቀርቀሪያ እሰብራለሁ፥ ነዋሪዎችዋንም ከአዌን ሸለቆ፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከዔደን ቤት አጠፋለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርከው ወደ ቂር ይሄዳሉ፥” ይላል ጌታ።