Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን ድል ነሣ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔርም ኢትዮጵያውያንን በአሳና በይሁዳ ፊት መታቸው፤ ኢትዮጵያውያኑም ሸሹ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔርም ኢትዮጵያውያንን እንዲያሸንፉ ዓሣንና ሠራዊቱን ረዳቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሳና በይ​ሁዳ ሕዝብ ፊት ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን መታ፤ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንም ሸሹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 14:12
17 Referencias Cruzadas  

የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይሁዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ ጌታ ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት ድል አደረጋቸው።


ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።


ስለዚህ እኔ በከንቱ እንደሚሮጥ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤


አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።


ጌታም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፤ በገባዖንም በጽኑ ውግያ ድል አደረጓቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በሆነው መንገድ ላይ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


“ጌታ በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።


የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።


ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡ በአሞንና በሙዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ ጌታ ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ተሸነፉ።


እርሱም ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ይዞ ነበር። ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም፤ እነርሱም የልብያ ሰዎች ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።


“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” ይላል ጌታ። “እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?


በዚህ ዓይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ፥ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ ወደ ሰዶም እና ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ይደርሳል።


እንዲህም ሆነ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚህ ቀን የጌታ ሠራዊት ሁሉ ከግብጽ ምድር ወጡ።


በዚያም ቀን ጌታ የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብጽ ምድር አወጣ።


ከእንስሶቻቸውም ኀምሳ ሺህ ግመሎች፥ ሁለት መቶ ኀምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህዮች፥ ከሰዎችም መቶ ሺህ ማረኩ።


በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎች ለጌታ ሠዉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios