ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ መንደር እስከ ታላቅ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት ጭምር እነርሱ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ ወረረ።
አሞጽ 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የእርሷንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በጋዛ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ መሠረቶችዋንም ትበላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ አዳራሾችዋንም ትበላለች። |
ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ መንደር እስከ ታላቅ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት ጭምር እነርሱ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ ወረረ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ለኤዶምያስ አሳልፈው ለመስጠት መላውን ሕዝብ ማርከው ወስደዋልና ስለ ሦስት የጋዛ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ነዋሪዎችዋን ከአዛጦን፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።