Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 39:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በማጎግ እና ያለ ስጋት በደሴቶች በሚቀመጡት ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በማጎግና ያለ ሥጋት በባሕር ዳርቻ በሚኖሩት ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በማጎግ ምድርና በባሕር ዳርቻዎች ሰዎች ያለ ስጋት በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ እሳት አቀጣጥላለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በማ​ጎ​ግም ላይ፥ በሰ​ላ​ምም በደ​ሴ​ቶች በሚ​ቀ​መጡ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በማጎግም ላይ ሳይፈሩም በደሴቶች በሚቀመጡ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 39:6
21 Referencias Cruzadas  

የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፥ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታትም ሁሉ፥ በባሕር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥


በግብጽ እሳትን አነድዳለሁ፥ ሲን ትጨነቃለች፥ ኖ ትሰባበራለች፥ ኖፍ በቀን ጠላቶች ያጠቁአታል።


እሳትን በግብጽ ሳነድድ፥ ረዳቶችዋም ሁሉ ሲሰበሩ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


በዚያ ቀን ያለ ስጋት የተቀመጠችውን ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መልእክተኞች ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ እንደ ግብጽም ቀን ጭንቀት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ መጥቷልና።


ጅማትንም አደርግላችኋለሁ፥ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ ቆዳ አለብሳችኋለሁ፥ በውስጣችሁ እስትንፋስ አገባባችኋለሁ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


እንዲህም ትላለህ፦ ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ፤ ያለ ሥጋት በሰላም ወደሚኖሩ፥ ሁሉም ሳይፈሩ ያለ ቅጥር፥ ያለ መወርወሪያና ያለ በር ወደሚቀመጡ እሄዳለሁ፤


ሳባ፥ ድዳን፥ የተርሴስ ነጋዴዎች፥ መንገዶችዋም ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን?


የሰው ልጅ ሆይ፥ የማጎግ ምድር፥ በሮሽ፥ በሜሼኽና በቱባል ላይ አለቃ ወደ ሆነው ወደ ጎግ ፊትህን አቅና፥ ትንቢትም ተናገርበት፥


ጎሜርንና ሠራዊቱ ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻ ያለው የቶጋርማ ቤትና ሠራዊቱ ሁሉ፥ ብዙ ሕዝቦችም ከአንተ ጋር አወጣለሁ።


አንተ በሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የእርሷንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”


በአዛሄልም ቤት ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የአዴርንም ልጅ የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።


በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የእርሷንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።


በቁጣው ፊት ማን ይቆማል? የቁጣውንስ ንዳድ ማን ይቋቋማል? መዓቱ እንደ እሳት ፈሰሰ፤ ከእርሱ የተነሣ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ።


ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን ለማሳትና ለጦርነት ለማስከተት ይወጣል፤ ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ ነው።


ወደ ምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ ነገር ግን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው።


ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos