2 ዜና መዋዕል 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቶና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቁ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ልትፈትነው መጣች፤ ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። ቅመማ ቅመም፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋራ ደረሰች፤ ወደ ሰሎሞንም ቀርባ በልቧ ያለውን ሁሉ አጫወተችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግሥተ ሳባ ስለ ሰሎሞን የሚነገረውን አስደናቂ ጥበብ ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ የእንቆቅልሽ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፤ ወደ ኢየሩሳሌም ስትመጣም ብዙ የክብር አጃቢዎችን አስከትላ ሽቶ፥ የከበሩ ዕንቆችና እጅግ የበዛ ወርቅ በግመሎች አስጭና ነበር፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኘች ጊዜ በሐሳብዋ የነበረውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው። |
እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ። ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ።
ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።”
ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ፥ እጅግም ብዙ ሽቶ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው፤ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ ሽቶ ከቶ አልነበረም።
የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ከከሳባ የሆኑት ሁሉ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፥ የጌታን ምስጋና ያወራሉ።
የደቡብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።
ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ፥ ዕጣንና ከርቤ አቀረቡለት።
ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ትነሳለች፥ በእነርሱም ላይ ትፈርዳለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ።
ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፥ “ጌታዬ ሆይ፤ አይደለም፤ እኔስ ልቧ ክፉኛ ያዘነባት ሴት ነኝ፤ የልቤን ኀዘን በጌታ ፊት አፈሰስሁ እንጂ፥ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም።