Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ዜና መዋዕል 1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ሰሎሞን ጥበብን መጠየቁ

1 የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ ላይ ራሱን አጸና፤ ጌታ አምላኩም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ እጅግም አገነነው።

2 ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ።

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የጌታ ባርያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው ወደ ኮረብታማው ስፍራ ሄዱ።

4 ለጌታ ታቦት ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ነበርና ዳዊት ከቂርያት-ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ስፍራ ታቦቱን አምጥቶት ነበር።

5 የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በጌታ ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንም ጉባኤውም ይህን ይፈልጉት ነበር።

6 ሰሎሞንም በጌታ ፊት በመገናኛው ድንኳን አጠገብ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጣ፥ በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።

7 በዚያም ሌሊት ጌታ፦ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ነገር ጠይቀኝ” ሲል ለሰሎሞን ተገለጠ።

8 ሰሎሞንም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅና ጽኑ ፍቅር አሳይተኸዋል፥ በእርሱም ፋንታ አንግሠኸኛል።

9 አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ! ቁጥሩ እንደ ምድር ትቢያ በሆነው በብዙ ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃልህ ይጽና።

10 አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት ለመውጣትና ለመግባት እንድችል ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማን ነው?”

11 ጌታም መልሶ ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ይህ በልብህ ነበረና፥ ባለጸግነትንና ሀብትን ክብርንና የጠላቶችህን ነፍስ ረጅምም ዕድሜን አልጠየቅህምና፥ ነገር ግን ባነገሥሁህ በሕዝቤ ላይ ለመፍረድ እንድትችል ጥበብንና እውቀትን ለራስህ ጠይቀሃልና፥

12 ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።”

13 ሰሎሞንም በገባዖን ካለው ከኮረብታው ስፍራ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ።


የንጉሥ ሰሎሞን ሠራዊትና የንግድ እንቅስቃሴ

14 ሰሎሞንም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፥ አንድ ሺህም አራት መቶ ሰረገሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሰረገሎች ከተሞችና ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።

15 ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቈላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ።

16 ሰሎሞንም ፈረሶችን ከግብጽና ከቀዌ አስመጣ፤ የንጉሡም ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ከቀዌ ያመጡአቸው ነበር።

17 አንዱም ሠረገላ በስድስት መቶ፥ አንዱም ፈረስ በመቶ ኀምሳ ሰቅል ብር ከግብጽ ያስመጡ ነበር፤ እነርሱም መልሰው ለኬጢያውያንና ለሶሪያ ነገሥታት ሁሉ ይልኩ ነበር።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos