Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ ላይ ራሱን አጸና፤ ጌታ አምላኩም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ እጅግም አገነነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አምላኩ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበር፣ እጅግም ስላገነነው፣ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በመንግሥቱ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የዳዊት ልጅ ንጉሥ ሰሎሞን መንግሥቱን አጠናከረ፤ እግዚአብሔር አምላኩም ባረከው፤ እጅግ በጣም ገናናም አደረገው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ በረታ፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ እጅ​ግም አከ​በ​ረው፤ አገ​ነ​ነ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ፤ እጅግም አገነነው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 1:1
17 Referencias Cruzadas  

ጌታም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።


ሰሎሞንም በአባቱ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ የመንግሥቱም ሥልጣን እጅግ የጸና ሆነ።


ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ።


በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፦ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፥


በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆች ስም የአንተን ስም ታላቅ አደርጋለሁ።


ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።


እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።


ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፥ ጌታ ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፥ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


እንደዚሁም የመንግሥቱ ነገርና ኃይሉ ሁሉ በእርሱም በእስራኤልም በአገሮችም መንግሥታት ሁሉ ላይ ያለፉት የታሪክ ክሰስተቶች ተጽፈዋል።


ብዙዎቹም ለጌታ መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፥ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።


አሳዳሪውም ጌታ ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወነለት ባየ ጊዜ፥


ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን እንዲያውቁ በዚህ ቀን አንተን በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ከፍ ከፍ ማድረግ እጀምራለሁ።


አሁንም፥ ልጄ ሆይ! ጌታ ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም እንደ ተናገረው ያከናውንልህ፥ የአምላክህንም የጌታን ቤት ሥራ።


የሚሠሩበት ወርቅና ብር ናስና ብረት ቍጥር የለውም፤ ተነሥተህ ሥራ፥ ጌታም ከአንተ ጋር ይሁን።”


ሰሎሞንም ለጌታ በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ፥ ተከናወነለትም፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios