2 ዜና መዋዕል 30:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም በጌታ አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ ያበረታታ ነበር። የአንድነትንም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ለሰባት ቀን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ማዕድ በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ በንግግሩ አበረታታ። በሰባቱም የቀን በዓል ቀናት እየበሉና የኅብረት መሥዋዕቱንም እያቀረቡ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር የተደረገውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በመምራት ከፍ ያለ ችሎታ ስላሳዩ ሌዋውያኑን አመሰገነ። ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ሰባት ቀን የኅብረት መሥዋዕት አቅርበው ከበሉ በኋላ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያንን ሁሉ ያጽናና ነበር። የደኅንነትም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ ያጽናና ነበር። የደኅንነትንም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ። |
እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለጌታም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤
አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ለሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ እንዲፈርዱ ዳኞችንና ፈራጆችን ሹምላቸው፥ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።
የአምላካችን መልካም እጅ በላያችን ላይ ስለ ነበረች፥ የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ ከሆነው ከማሕሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሼሬብያን፥ ከእርሱም ጋር ዐሥራ ስምንት ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን።
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕዝራ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛው ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።
በየስፍራቸውም ቆመው የጌታ አምላካቸውን የሕግ መጽሐፍ የቀኑ ሩብ ያህል አነበቡ፥ የቀኑ ሩብ ደግሞ እየተናዘዙና፥ ለጌታ አምላካቸው እየሰገዱ አሳለፉ።
እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥
ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”