Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የእስራኤል ሕዝብ ለብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ ሕግና ያለ አስተማሪ ካህን ይኖር ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እስ​ራ​ኤ​ልም ብዙ ዘመን እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ሳያ​መ​ልኩ፥ ያለ አስ​ተ​ማ​ሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖ​ራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 15:3
22 Referencias Cruzadas  

ገዢው ነህምያ፥ ጸሐፊው ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡን የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህ ቀን ለጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነው፤ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።


ጌታም በሙሴ አንደበት የነገራቸውን ሥርዓት ሁሉ ለእስራኤል ልጆች እንድታስተምሩ ነው።”


የካህን ከንፈሮች ዕውቀትን መጠበቅ አለባቸው፤ ሰዎችም ሕግን ከአፉ መፈለግ አለባቸው፤ ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ መልእክተኛ ነው።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤


ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።


ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግ እያላቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤


ሥርዓትህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፥ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባሉ።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥


እነርሱ ራሳቸው ስለ እኛ በእናንተ መካከል ምን ዓይነት አቀባበል ተደርጎልን እንደ ነበር፥ ሕያውም የሆነውን እውነተኛ አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ፥


ሕግ የሌላቸውን ለመጠቅም ስል፥ የእግዚአብሔር ህግ ሳይኖረኝ ቀርቶ ሳይሆን በክርስቶስ ሕግ ስር ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለኝ ሆንኩ።


የዘለዓለም ሕይወትም ይህች ናት፤ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንከውን አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ነው።


ጌታም አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


በነገሠም በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች እንዲያስተምሩ መሳፍንቱን፥ ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልን፥ ሚክያስን፥ ላከ።


“እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምልክበት ዘመን እየመጣ ነው፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እርሱም፦ የጌታን ቃላት ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም።


ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ፤ ሰበረም፤ ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ፥ ነቢዮችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios