2 ዜና መዋዕል 29:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያውም ወር የጌታን ቤት ደጆች ከፈተ፥ አደሳቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሮች ከፈተ፤ አደሳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ በነገሠበት ዓመት በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በር ሁሉ እንደገና ከፍቶ አደሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንግሥቱም በጸና ጊዜ በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤት ደጆች ከፈተ፤ አደሳቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያውም ወር የእግዚአብሔርን ቤት ደጆች ከፈተ፤ አደሳቸውም። |
በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ይቀድሱ ጀመር፥ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ ጌታ ቤት ዋና የመግቢያ ደጅ ደረሱ የጌታንም ቤት በስምንት ቀን ውስጥ ቀደሱት፥ በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ።
ደግሞም ዋና የመግቢያ ደጆችን ዘጉ፥ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፥ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።
በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በዓሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረፁትና ቀልጠው ከተሰሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር።