2 ዜና መዋዕል 34:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በዓሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረፁትና ቀልጠው ከተሰሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በዘመነ መንግሥቱ በስምንተኛው ዓመት ገና ወጣት ሳለ፣ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ፤ በዐሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኰረብታ መስገጃ ስፍራዎች፣ ከአሼራ፣ ምስል ዐምዶች፣ ከተቀረጹ ጣዖታትና ቀልጠው ከተሠሩ ምስሎች አነጻ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ኢዮስያስ በነገሠ በስምንተኛ ዓመቱ፥ ገና ወጣት ሳለ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን አምላክ እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመረ፤ ከአራት ዓመት በኋላም የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራ የሴት አምላክ ምስሎችንና ሌሎችን ጣዖቶች ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ማስወገድ ጀመረ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመረ፤ በዐሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታውና ከዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹትና ቀልጠው ከተሠሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በአሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹትና ቀልጠው ከተሰሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር። Ver Capítulo |