2 ዜና መዋዕል 29:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ይቀድሱ ጀመር፥ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ ጌታ ቤት ዋና የመግቢያ ደጅ ደረሱ የጌታንም ቤት በስምንት ቀን ውስጥ ቀደሱት፥ በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ማንጻቱንም በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን ጀምረው በዚያ ወር በስምንተኛው ቀን እስከ መቅደስ ሰበሰብ ደረሱ፤ በሚቀጥሉትም ስምንት ቀናት የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቀደሱ፤ የመቀደሱም ሥራ በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ስድስተኛው ቀን ተጠናቀቀ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የማንጻቱ ሥራ በመጀመሪያው ወር መባቻ ቀን ተጀምሮ በስምንተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ የሚያስገባው ክፍል ጭምር ሙሉ በሙሉ ተፈጸመ፤ ከዚህ በኋላም ቤተ መቅደሱን ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት ለማዘጋጀት በተከታዮቹ ስምንት ቀኖች ማለትም ወሩ በገባ እስከ ዐሥራ ስድስተኛው ቀን ድረስ ሠሩ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በስምንት ቀን አነጹ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ይቀድሱ ጀመር፤ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በስምንት ቀን ቀደሱ፤ በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ። Ver Capítulo |