ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።
2 ዜና መዋዕል 24:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ በንጉሡና በዮዳሄ ፊት አመጡ፤ በእርሱም ለጌታ የቤት ዕቃ፥ የአገልግሎትና የቁርባን ዕቃ፥ ሙዳዮቹም፥ የወርቅና የብርም ዕቃ ተሠራበት። በዮዳሄም ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጨረሱም በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ዮዳሄ አመጡ፤ በገንዘቡም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ማለትም ለአገልግሎትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚውሉ ዕቃዎች እንደዚሁም ጭልፋዎችና ሌሎች የወርቅና የብር ዕቃዎችም ተሠሩ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ይቀርብ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእድሳቱ ሥራ ባለቀ ጊዜም ቀሪው ገንዘብ ለንጉሥ ኢዮአስና ለካህኑ ዮዳሄ ተሰጠ፤ እነርሱም በዚህ ወርቅ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎትና ለመሥዋዕት የሚውሉ ሳሕኖችንና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ገዙ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ ዘወትር በቤተ መቅደስ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ካህኑ ኢዮአዳ ፊት አመጡ፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር ቤት ዕቃ፥ ለአገልግሎትና ለቍርባን ዕቃ፥ ለጭልፋዎችም፥ ለወርቅና ለብርም ዕቃ አደረጉት። በኢዮአዳም ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ በንጉሡና በዮዳሄ ፊት አመጡ፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር ቤት ዕቃ፥ ለአገልግሎትና ለቍርባን ዕቃ፥ ለጭልፋዎችም፥ ለወርቅና ለብርም ዕቃ አደረጉት። በዮዳሄም ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር። |
ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፦ “ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ፥ የሚቀመጥበትንም ቤት ለመሥራት የዝግባ እንጨት እንደ ላክኽለት፥ እንዲሁ ለእኔ አድርግ።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በጌታ ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑም ክብርም እንዲሰጡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።