Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 7:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ከጥሩ ወርቅም የተሠሩትን ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶቹንና ጭልፋዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም፥ ለውስጠኛውም ቤት ለቅድስተ ቅዱሳን ደጆች ለቤተ መቅደሱም ደጆች የሚሆኑትን የወርቅ ማጠፊያዎች አሠራ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 7:50
11 Referencias Cruzadas  

ሆኖም ከብር ለሚሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያ፥ ጐድጓዳ ወጭት፥ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርም ሆነ ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅድሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም።


ጽናዎችንና ዱካዎችን ከብርና ከወርቅ የተሠሩ በመሆናቸው ወሰዱአቸው።


ለማፍሰሻም እንዲሆኑ ወጭቶችዋን ጭልፋዎችዋንም መቅጃዎችዋንም ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።


መኮስተሪያዎችዋንና የኩስታሪ ማስቀመጫዎችዋን ከንጹሕ ወርቅ ሥራ።


አመድ የሚጠራቀምባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹን፥ ድስቶቹን፥ ሜንጦቹንና ማንደጃዎቹን ታደርጋለህ፤ ዕቃዎቹ ሁሉ ከነሐስ ሥራ።


የዘበኞቹም አለቃ ወጭቶቹንና ማንደጃዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹንና የሸክላ ድስቶቹን፥ መቅረዞችንና ሙዳዮችን መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ።


በመቅደሱ ፊት ያለውን ርዝመቱን ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፦ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።


በጌታም ፊት ካለው መሠዊያ ላይ ያለውን የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶ ያመጣል፥ ከተወቀጠውም ከመዐዛው ያማረ ዕጣን በሁለቱ የእጁ መዳፎች ሙሉ ዘግኖ ይወስዳል፤ ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፦ “ለጌታ የተቀደሰ” ተብሎ ይጻፋል። በጌታም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


ዕጣንም የተሞሉት ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ሙዳዮች፥ እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል ነበሩ፤ የሙዳዮቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos