ጌታም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማነው?’ አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ ያቀርቡ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለ፦ ‘ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ እንዲወድቅ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ያታለለው ማን ነው?’ አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ ‘የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት ማን ያሳስተው?’ አለ። “አንዱ አንድ ሐሳብ፣ ሌላውም ሌላ ሐሳብ አቀረበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማን ነው?’ ሲል ጠየቀ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ አቀረቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው?” አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ‘ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው?’ አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ። |
ጌታም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማነው?’ አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ ያቀርቡ ነበር።
በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ።
እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ ‘ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ።’ ጌታም እንዲህ አለው፦ ‘ታታልለዋለህ፤ ይከናወንልሃል፤ ውጣ፥ እንዲህም አድርግ።
ነቢዩ ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ ጌታ ነኝ፥ በእርሱም ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከልም አጠፋዋለሁ።