Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 25:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ብትሄድ ግን፥ በእነርሱም ማሸነፍን ብታስብ፥ የመርዳትና የመጣል ኃይል ከጌታ ዘንድ ነውና ጌታ በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሄደህ፣ ጦርነቱን በቈራጥነት ብትዋጋም እንኳ፣ የመርዳትና የመጣል ኀይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “አንተ በዚህ በምታደርገው ጦርነት የእስራኤል ወታደሮች ድጋፍ ይሆኑኛል ብለህ ታስብ ይሆናል፤ ነገር ግን አሸናፊም ሆነ ተሸናፊ እንድትሆን የሚያደርግህ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እነሆ አሁንም እርሱ በጠላቶችህ ድል እንድትሆን ያደርግሃል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ብት​ሄድ ግን፥ በእ​ነ​ር​ሱም ማሸ​ነ​ፍን ብታ​ስብ፥ የማ​ጽ​ና​ትና የመ​ጣል ኀይል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት ይጥ​ል​ሃል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ብትሄድ ግን፥ በእነርሱም ማሸነፍን ብታስብ፥ የመርዳትና የመጣል ኃይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል” አለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 25:8
25 Referencias Cruzadas  

አሳም እንዲህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ።”


እርሱም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ! በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፥ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።


አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያሟላላችኋል።


ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ፍልምያ ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ሀብትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።


የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።


ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፥ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኩራ።


ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በጉልበቱ አያመልጥም።


ጌታ የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።


የዳዊት መዝሙር። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።


ጌታ የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፥ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፥ በቀኙ ብርታት ማዳን አለና።


“እግዚአብሔር ቁጣውን አይመልስም፥ ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ።


እርሱ ቢያቈስልም ይጠግናልና፥ ቢሰብርም፥ እጆቹ ይፈውሳሉና።


ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት እንሂድን? ወይስ ልቅር?” አለው። እርሱም መለልሶ እንዲህ አለው፦ “ውጣ፥ ይከናወንልህ፤ በእጅህም ተላልፈው ይሰጣሉ።”


ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።”


ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።


ጌታም ጌዴዎንን፥ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችሃለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደየመጡበት ይመለሱ” አለው።


ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


ከዚህ በኋላ ወደ ደቀመዛሙርቱ መጥቶ እንዲህ አላቸው “ከእንግዲህስ ተኙ፥ ዕረፉም፤ እነሆ ሰዓቱ ቀርቦአል፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል።


እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው።


የተቃዋሚዎቹን ቀኝ ከፍ ከፍ አደረግህ፥ ጠላቶቹንም ሁሉ ደስ አሰኘህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios