2 ዜና መዋዕል 25:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 አንተም፦ ‘እነሆ፥ ኤዶምያስን መትቻለሁ’ ብለህ ኰርተሃል፤ በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተ ከይሁዳ ጋር አብረህ ለመውደቅ ለምን መከራ ትሻላህ?” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እነሆ፤ ኤዶምን አሸንፌአለሁ ብለህ ልብህ በትዕቢት ተወጥሯል፤ አሁን ክብርህን ጠብቀህ ዐርፈህ በቤትህ ተቀመጥ! ጠብ በመጫር በራስህና በይሁዳ ላይ ውድቀት ለማምጣት ችግር የምትፈጥረው ለምንድን ነው?” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 አሜስያስ ሆይ፥ እነሆ አንተም ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ ይልቅስ በቤትህ ዐርፈህ ብትቀመጥ የሚሻልህ መሆኑን እመክርሃለሁ፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍትን የሚያስከትል ነገር ለመቈስቈስ ስለምን ትፈልጋለህ?” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 አንተም፦ እነሆ፥ ኤዶምያስን መትቻለሁ ብለህ በልብህ ኰርተሃል፤ በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተ ከይሁዳ ጋር ትወድቅ ዘንድ ስለምን መከራን በራስህ ትሻለህ?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 አንተም ‘እነሆ፥ ኤዶምያስን መትቻለሁ’ ብለህ ኵርተሃል፤ በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተ ከይሁዳ ጋር ትወድቅ ዘንድ ስለ ምን መከራ ትሻላህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ። Ver Capítulo |