ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”
2 ዜና መዋዕል 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ገና ሕፃን ሳለ፣ ምንም ማድረግ በማይችልበትና እነርሱንም ለመቋቋም ዐቅሙ በማይፈቅድለት ጊዜ የማይረቡ ምናምንቴዎች በዙሪያው ተሰበሰቡበት፣ በረቱበትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉዎች ሰዎችና የሕግ ተላላፊዎች ልጆችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃን በነበረና በልቡ ድፍረት ባልነበረው ጊዜ፥ ሊቋቋመውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረታበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት። |
ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”
የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት።
እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”
እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “በዳዊት ዘንድ ምን ድርሻ አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ! ወደ እየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ! አሁን ቤትህን ተመልከት።” እስራኤልም ሁሉ ወደ እየድንኳኖቻቸው ሄዱ።
ንጉሡም ሮብዓም በኢየሩሳሌም በረታ ንጉሥም ሆነ፤ ሮብዓምም በነገሠ ጊዜ የአርባ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ ጌታም ስሙን እንዲያኖርባት ከእስራኤል አገር ሁሉ በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የአሞን ሴት ናዕማ ነበረች።
አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፤ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤
እስከ አሁን በነበረው ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ እንደገና የእግዚአብሔር ቃላት የመጀመሪያውን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።