Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “እንግዲህ አሁን እናንተ እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁና፥ ኢዮርብዓምም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ እምቦሶች ከእናንተ ጋር ናቸውና በዳዊት ልጆች እጅ የሚሆነውን የጌታን መንግሥት ልትቋቋሙ ታስባላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “አሁንም እናንተ በዳዊት ዘርዐ ትውልድ እጅ ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ልትቋቋሙ ዐስባችኋል። በርግጥም በሰራዊት ረገድ እጅግ ብዙ ናችሁ፤ አማልክታችሁ ይሆኑ ዘንድ ኢዮርብዓም የሠራቸውንም የወርቅ ጥጆች ይዛችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አሁንም እናንተ እግዚአብሔር ለዳዊት ዘሮች የሰጠውን የመንግሥት ሥልጣን በመድፈር ለመቃወም ዐቅዳችኋል፤ ይህ ዕቅዳችሁ ግቡን እንዲመታ ለማድረግም እጅግ ብዙ የሆነ የጦር ሠራዊት አሰልፋችኋል፤ ለእናንተ አማልክት እንዲሆኑ ኢዮርብዓም ከወርቅ ያሠራቸውን የጥጃ ምስሎች ይዛችሁ መጥታችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁ​ንም በዳ​ዊት ልጆች እጅ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ልት​ቋ​ቋሙ እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ። እና​ን​ተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም አማ​ል​ክት አድ​ርጎ የሠ​ራ​ላ​ችሁ የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶች ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አሁንም በዳዊት ልጆች እጅ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ልትቋቋሙ ታስባላችሁ። እናንተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፤ ኢዮርብዓምም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ እምቦሶች ከእናንተ ጋር ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:8
15 Referencias Cruzadas  

በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዓይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።


ከዚህም በኋላ ከወርቅ የተሠሩት ሁለት የኰርማ ምስሎች አንዱን በቤትኤል፥ ሁለተኛውንም በዳን አቆመ።


ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችና ከብረት የተቀረጹ ምስሎችን ለማምለክ በመሥራትህ ቁጣዬን አነሣሥተሃል፤


እርሱ ግን ለኮረብታው መስገጃዎች ለአጋንንቱም ለሠራቸውም እምቦሶች ካህናትን ሾመ።


አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”


እርሱም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ! በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፥ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።


በአምላክህ በጌታ ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ሊያስቀምጥህ የወደደህ አምላክህ ጌታ ብሩክ ይሁን፤ አምላክህ እስራኤልን ለዘለዓለም ሊያጸናቸው ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድና ጽድቅ እንድታደርግ በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”


ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በጉልበቱ አያመልጥም።


የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና ‘ይህ በላያችን እንዲነግሥ አንፈልግም፤’ ብለው በኋላው መልእክተኞችን ላኩ።


ነገር ግን እነዚያን በላያቸው እንድነግሥ ያልፈለጉትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው፤ በፊቴም እረዱአቸው።’”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos