1 ጢሞቴዎስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይሰክር፥ የማይቆጣ ነገር ግን ታጋሽ የሆነ፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ገንዘብን የማያፈቅር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማይሰክር፣ የማይጣላ ግን ጨዋ የሆነ፣ የማይጨቃጨቅ፣ ገንዘብንም የማይወድ ሊሆን ይገባዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማይሰክር፥ ክርክር የማይወድ፥ ገር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ገንዘብን የማያፈቅር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ |
ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!
እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።
“ከታናናሾቻቸው ጀምሮ እስከ ታላላቆቻቸ ድረስ ሁሉም በግፍ ለሚገኝ ጥቅም ስስታም ናቸውና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ተንኰልን ይፈጽማሉ።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉም በግፍ ለሚገኝ ጥቅም ስስታም ነውና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
“እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤
በነፋስና በውሸት የሚሄድ፥ ሐሰትንም የሚናገር፥ “ስለ ወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ስብከት እናገርልሃለሁ” የሚል ሰው ቢኖር፥ እርሱ የዚህ ሕዝብ ሰባኪ ይሆናል።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።
“በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ መካከል በሮችን የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። ቁርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም።
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉምና፤ በሚያሳምን ንግግርና በሽንገላ የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።
ሰዎች እንዲህ ይሆናሉና፤ ራሳቸውን የሚወዱ፥ ገንዘብን ወዳጆች፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥
ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤
ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!
እኔ ዮሐንስ፥ ከእናንተ ጋር አብሬ በኢየሱስ መከራውንና መንግሥቱንና ጽናቱን የምካፈል ወንድማችሁ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።