Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉምና፤ በሚያሳምን ንግግርና በሽንገላ የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንደእነዚህ ዐይነቶቹ ሰዎች ራሳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉም። በለዘቡና በሚያቈላምጡ ቃላት የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና፥ በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 16:18
54 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎም ፍርድ ለማግኘት ወደ ንጉሡ ለሚመጣ እስራኤላዊ ሁሉ አቀራረቡ እንዲህ ነበር፤ ስለዚህ አቤሴሎም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።


የእስራኤልም ንጉሥ አራት መቶ ነቢያትን ሰብስቦ፦ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት እንሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ” አሉት።


የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙሪቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፥ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።


የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፥ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።


ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፥ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዱና ይጐዳሉ።


እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥ እናንተም ሞኞች አስተውሉ።


ለሚንቁኝ ሁልጊዜ፦ ጌታ፦ ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል ይላሉ፤ በልቡም እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም ይላሉ።


እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገሩ፥ ሰላም ሳይኖር የሰላምን ራእይ ያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።


ጌታ ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፦ ሰው ሲያበላቸው “ሰላም አለ” ይላሉ፤ ካላበላቸው ግን ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።


“በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ መካከል በሮችን የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። ቁርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም።


ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤


ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳት ታላላቅ ምልክትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።


“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፥ በውስጣቸው ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው።


የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።


እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገልግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።


መታዘዛችሁ በሁሉም ሰው ዘንድ ደርሶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።


ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ሊኖራችሁ ከሚገባ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትርቁ ብዬ እፈራለሁ።


የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።


የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።


አሁን ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሳምናለሁን? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? እስከ አሁን ሰውን ደስ የማሰኝ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ ባርያ አልሆንም ነበር።


የተቀሩት ሁሉ ግን የክርስቶስ ኢየሱስን ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅም የሚሹ ናቸውና።


መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው ምድራዊ ነው።


ይህንንም የምለው ማንም አሳማኝ በሚመስል ንግግር እንዳያታልላችሁ ብዬ ነው።


ይህንንም ስታደርጉ ከጌታ የርስትን ሽልማት እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው።


እንዲሁም ለመዳን እውነቱን ወድደው ባለ መቀበላቸው ለሚጠፉት በማታለል ክፋት ሁሉ ይመጣባቸዋል።


አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ ጭቅጭቅን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን መምሰል ሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!


የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያና የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዱትና በኢየሱስ ክርስቶስም ለተጠበቁት፥ ለተጠሩት፤


እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤


እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ የሚያማርሩ፥ ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው የትዕቢት ቃልን ይናገራል፤ለጥቅማቸው ሲሉ ሰዎችን ያደንቃሉ።


በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፤ መልአኩንም ልኮ ራእዩን ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ገለጠ፤


በማደሪያዬ እንዲያቀርቡት ያዘዝሁትን መሥዋዕቴንና ቁርባኔን ስለምን ረገጣችሁ? ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቁርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር፥ ከእኔ ይልቅ ለልጆችህ ስለምን ክብር ሰጠህ?’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos