La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለጦርነት አሰባስበው፥ በይሁዳ ምድር በሰኮ ላይ አከማቹ፤ በሰኮና በዓዜቃ መካከል ባለው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍልስጥኤማውያን ሰራዊታቸውን ለጦርነት አሰባስበው፣ በይሁዳ ምድር በሦኮን ላይ አከማቹ፤ እነርሱም በሰኰትና በዓዜቃ መካከል ባለው በኤፌሰደሚም ሰፈሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍልስጥኤማውያን ሶኮ ተብላ በምትጠራው በይሁዳ ለጦርነት ተሰለፉ፤ እነርሱም በሶኮና በዐዜቃ መካከል ኤፌስዳሚም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፍረው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለጦ​ር​ነት ሰበ​ሰቡ፤ ራሳ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ በሰ​ኮት ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሰ​ኮ​ትና በዓ​ዜቃ መካ​ከል በኤ​ፌ​ር​ሜም ሰፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን በይሁዳ ባለው በሰኮት አከማቹ፥ በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በአርፌስደሚም ሰፈሩ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 17:1
11 Referencias Cruzadas  

እርሱ ከዳዊት ጋር በፈስደሚም ነበረ፥ በዚያም ገብስ በሞላበት እርሻ ውስጥ ፍልስጥኤማውያን ለውጊያ ተሰብስበው ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ።


እንዲሁም ቤት-ጹርን፥ ሦኮን፥ ዓዶላምን፥


ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።


እንዲህም የተናገረው የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ የቀሩትን ለኪሶንና ዓዜቃንን በወጋ ጊዜ ነበር፤ ከተመሸጉት ከይሁዳ ከተሞች መካከል የተረፉት እነዚህ ብቻ ነበሩና።


የርሙት፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥


እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማትስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።


ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።


ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ተመለሱ።


በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ከባድ ጦርነት ነበረ፤ ሳኦልም ብርቱ ወይም ጀግና ሰው ባየ ቍጥር ወደ ራሱ ይሰበስብ ነበር።


ፍልስጥኤማውያንም እስራኤል በምጽጳ መሰብሰባቸውን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ሊወጓቸው ወጡ። እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ።