Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማትስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እነዚህም አሕዛብ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበኣልአርሞንዔም ተራራ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዊያውያን።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 3:3
31 Referencias Cruzadas  

ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል፥ እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል፥ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ድረስ ነው።


ከዚያ ወደ ጢሮስ ምሽግ፥ ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች፥ በይሁዳ ደቡብ ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ።


በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።


ከእስራኤል ሕዝብ ያልሆኑትን ከአሞራውያን፥ ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤው ያውንና ከኢያቡሳውያን ሕዝቦች ሁሉ የተረፉትን፥


የምዕራቡ ድንበር ከደቡቡ ድንበር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል። ይህም የምዕራቡ ድንበር ነው።


በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።”


ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ የወሰን ምልክት ታደርጋላችሁ የድንበራችሁም መጨረሻ በጽዳድ ይሆናል፤


ተመልሳችሁ ተጓዙ፥ ወደ ተራራማው ወደ አሞራውያን አገር፥ ወደ አጎራባቾቹም በዓረባም በደጋውና በቆላው ሁሉ፥ በኔጌብም በባሕርም ዳር ወዳሉ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም እስከ ታላቁ ወንዝም እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።


የሔርሞንን ተራራ ሲዶናውያን ሢርዮን ብለው ሲጠሩት፥ አሞራውያን “ሠኒር” ብለው ሰይመውታል።


በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር ከእስራኤል ልጆች ጋር ዕርቅ ያደረገች አንዲት ከተማ አልነበረችም፤ ሁሉንም በጦርነት ድል አድርገው ያዙ።


በምሥራቅና በምዕራብም ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞራዊውም፥ ወደ ኬጢያዊውም፥ ወደ ፌርዛዊውም፥ በተራራማውም አገር ወዳለው ወደ ኢያቡሳዊው፥ ከአርሞንዔምም በታች በምጽጳ ወዳለው ወደ ኤዊያዊው ላከ።


በግብጽ ፊት ለፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ናቸው፥ የኤዋውያን የሆኑትም እንዲሁ፥


የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይም መውጫ በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው በኣልጋድ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥


ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።


የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያን እንዲህ አሉአቸው፦ “ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ እንደሆነ እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን?”


ሲዶናውያን፥ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን?


የጌታ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በፍልስጤማውያንና በአሞናውያን እጅም አሳልፎ ሰጣቸው፤


በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።


ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።


ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው።


ስለዚህም ጌታ በሐጾር ሆኖ ይገዛ ለነበረው ለከነዓን ንጉሥ ለያቢን አሳልፎ ሰጣቸው። የያቢን ሠራዊት አዛዥ፥ በሐሮሼትሐጎይም የሚኖረው ሲሣራ ነበረ።


ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።


የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመቶና በሺህ ሆነው ሲዘምቱ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከአኪሽ ጋር ደጀን ሆነው ይከተሉ ነበር።


አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎችም ይህን ተመልክተው፥ በዚያው ዕለት ወደ ዔቅሮን ተመለሱ።


የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።


እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos