1 ነገሥት 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር የጌታን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአራት መቶ ሰማንያ ዓመት፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዚፍ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ አራት ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ። |
ትእዛዝህንም ምስክርህንም ሥርዓትህንም እንዲጠብቅ፥ ይህንንም ነገር ሁሉ እንዲያደርግ ያዘጋጀሁለትንም ቤት እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ልብ ስጠው።”
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የጣለው መሠረት ይህ ነው፤ ርዝመቱም በዱሮው መለክያ መሠረት ስልሳ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ ነበረ።
የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን።
በሩቅ ያሉትም መጥተው የጌታን መቅደስ ይሠራሉ፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የጌታን ቃል በእውነት ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።
ጌታም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ነገር ግን ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ ስለሚሆነው መልካም ነገር፥ በምትበልጠውና በምትሻለው፥ በእጆችም ባልተሠራች፥ እርሷም ከፍጡራን ባልሆነች ድንኳን፥
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረበት በዚያን ጊዜ ስለምን አልወሰዳችኋቸውም?