ዕዝራ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 የሰጡን መልስ ይህ ነው፤ “እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፤ አሁንም እንደ ገና የምንሠራው ቤተ መቅደስ፣ ከብዙ ዘመናት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ የጨረሰውን ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 “እነርሱም እንዲህ ሲሉ አስረድተውናል፤ ‘እኛ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የታላቁ እግዚአብሔር አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ለእርሱ ከብዙ ዘመን በፊት በአንድ ታላቅ የእስራኤል ንጉሥ ተሠርቶለት የነበረውን ቤተ መቅደስና ቅጽር እንደገና መልሰን በመሥራት ላይ እንገኛለን፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽሞላቸው የነበረውን ቤት እንሠራለን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ ‘እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፤ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። Ver Capítulo |