1 ነገሥት 11:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ሞተ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓምም በአባቱ በሰሎሞን እግር ተተክቶ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በርሱ ፈንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ሞተ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በአባቱ በሰሎሞን እግር ተተክቶ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፥ በአባቱም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በፋንታው ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በፋንታው ነገሠ። |
ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ልጁ አቢያ ተተክቶ ነገሠ። የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።
ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።
መንገሥም በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተ፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልቀበሩትም።
ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ እነርሱም፦ “ለምጻም ነው” ብለው ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ጠቢብ ወይም አላዋቂ እንደሚሆን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ከፀሐይ በታች በደከምሁበትና ጠቢብ በሆንሁበት በድካሜ ሁሉ ላይ ይሠለጥንበታል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።