1 ነገሥት 1:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ዐብረውት እንዲሄዱ አድርጓል፤ እነርሱም በንጉሡ በቅሎ አስቀመጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም እርሱን ያጅቡት ዘንድ ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄን ልጅ በናያንና የቤተ መንግሥቱን ክብር ዘበኞች ልኮአል፤ እነርሱም ንጉሡ በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ እንዲቀመጥ አድርገውታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፤ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካሁኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ሰደደ፤ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት። |
አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ ወጡ፤ የቢክሪ ልጅ ሼባዕን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፥ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፥ ከተማይቱም አስተጋባች፥ የሰማችሁትም ድምፅ ይህ ነው።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን፦ “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የጌታም ቃል ኪዳን ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል” አለው።