የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
1 ዜና መዋዕል 6:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣ የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕልቃና፥ ይሮሐም፥ ኤሊኤል፥ ቶሐ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕልቃና ልጅ፥ የይሮዓም ልጅ፥ የኤላኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥ |
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
አሮንም ለማስተስረይ ወደተቀደሰው ስፍራ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤተሰቡም፥ ለእስራኤል ጉባዔ ሁሉ አስተስርዮ እስኪ ወጣ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ማንም ሰው አይገኝ።
በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ።