Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 24:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የአሮንም ልጆች አመዳደብ ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደሚከተለው ነበረ፤ የአሮን ልጆች ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የአሮን ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ አሮን አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የአ​ሮ​ንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአ​ሮን ልጆች ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 24:1
16 Referencias Cruzadas  

አሮንም የዓሚናዳብን ልጅ የናሕሾንን እኅት ኤሊሼባን አገባ፥ እርሷም ናዳብ፥ አቢሁ፥ ኤልዓዛርንና ኢታማርን ወለደችለት።


ዳዊትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድሶንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራሪም በየሰሞናቸው ከፈላቸው።


ለአሮንም ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ተወለዱለት።


እነዚህ የአሮን ልጆች ስሞች ናቸው፤ በኩሩ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር።


የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ነበሩ። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።


ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ።


የካህናቱንና የሌዋውያኑንም ክፍላቸውን በጌታም ቤት ለሚያገልግሉበት ሥራ ሁሉ አስታወቀው። በጌታም ቤት ለሚያገለግሉበት ዕቃ ሁሉ፥


ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ ሁሉም ተቀድሰው ነበር፥ በሰሞናቸውም አልተከፈሉም ነበር፤


የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።


ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ዮዳሄ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ዮዳሄ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ በሰንበት ቀን ይገቡ የነበሩትን በሰንበትም ቀን ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ።


ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በጌታ ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑም ክብርም እንዲሰጡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።


በሙሴም መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕረጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቡአቸው።


ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በጌታ ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ በጌታ ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር።


የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥


የአቢሹዓ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኤልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios