1 ዜና መዋዕል 29:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን፣ ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናሱ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ሥራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤት ወርቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረትን፥ እንጨትን፥ ደግሞም መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እንደ ጕልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዐይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ። |
ትእዛዝህንም ምስክርህንም ሥርዓትህንም እንዲጠብቅ፥ ይህንንም ነገር ሁሉ እንዲያደርግ ያዘጋጀሁለትንም ቤት እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ልብ ስጠው።”
ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።