Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 29:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ንጉሡም ዳዊት ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በብቸኛነት እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ብላቴና ለጋ ነው፤ ሕንጻው ግን ለጌታ ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር አምላክ በመሆኑ፣ ሥራው ከባድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ንጉሡ ዳዊ​ትም ለጉ​ባ​ኤው ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን የመ​ረ​ጠው ልጄ ሰሎ​ሞን ገና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ሕን​ጻው ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላክ ነው እንጂ ለሰው አይ​ደ​ለ​ምና ሥራው ታላቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ንጉሡም ዳዊት ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ “እግዚአብሔር ብቻውን የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ብላቴና ለጋ ነው፤ ሕንጻው ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 29:1
17 Referencias Cruzadas  

ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”


አሁንም፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል።


አቤቱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል።


ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች እንዲወቅሩ ጠራቢዎችን አኖረ።


ዳዊትም እንዲህ ብሏልና፦ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለጌታም የሚሠራው ቤት በአገሩ ሁሉ በስሙና በክብሩ እጅግ ታላቅና ዝነኛ ሊሆን ይገባል፤ እኔም ስለዚህ ዝግጅትን አደርጋለሁ።” ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ የግንባታ ቁሳቁስ አዘጋጀ።


ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የሠራዊቱ አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆቹ ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


አሁንም፥ እነሆ፥ ጌታ ለመቅደስ የሚሆን ቤትን እንድትሠራ መርጦሃልና በርትተህ በቈራጥነት ፈጽመው።”


አሁንም የጌታ ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱ፥ ለልጆቻችሁም ለዘለዓለም እንድታወርስዋት የአምላካችሁን የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፥ ፈልጉም።


ትእዛዝህንም ምስክርህንም ሥርዓትህንም እንዲጠብቅ፥ ይህንንም ነገር ሁሉ እንዲያደርግ ያዘጋጀሁለትንም ቤት እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ልብ ስጠው።”


ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ።


ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።


እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማይቱም በጉብታዋ ላይ ዳግም ትሠራለች፥ የንጉሡ ቅጥርም ዱሮ በነበረበት ቦታ ላይ ይታነጻል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos