1 ዜና መዋዕል 2:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኩሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይራሕመኤል ወንድም የነበረው የካሌብ በኲር ልጅ ስሙ ሜሻዕ ይባል ነበር፤ ይህም ሜሻዕ ዚፍ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዚፍም ማሬሻን ወለደ፤ ማሬሻም ኬብሮንን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያሬምሄል ወንድም የካሌብ ልጆች በኵር የዚፍ አባት ማሪስ ነው፤ የኬብሮንም አባት የማሪስ ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኵሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ። |
የዚፍ ሰዎች ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል ወጥተው፦ “እነሆ፤ ዳዊት ከየሴሞን በስተ ደቡብ በሐኪላ ኰረብታ ላይ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቆ ይገኛል።