Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ዜና መዋዕል 8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የብንያም ትውልድ

1 ብንያምም በኩሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፥

2 አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ።

3 ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም አዳር፥ ጌራ፥ አቢሁድ፥

4 አቢሱ፥ ናዕማን፥ ኦሖዋ፥

5 ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም ናቸው።

6 እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ወደ መናሐትም ተማረኩ፤

7 ናዕማን፥ አኪያ፥ ሔግላ የተባለው ጌራ ዖዛንና አሒሑድን ወለደ።

8 ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን እንዲሄዱ ካሰናበተ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ።

9 ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥

10 ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።

11 ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ።

12 የኤልፍዓልም ልጆች፤ ዔቤር፥ ሚሻም አኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ ነበሩ፤

13 በሪዓና ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤

14 አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥

15 ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥

16 ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ የበሪዓ ልጆች ነበሩ።

17 ዝባድያ፥ ሜሱላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፥

18 ይሽምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ የኤልፍዓል ልጆች ነበሩ።

19 ያቂም ዝክሪ፥ ዘብዲ፥

20 ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥

21 ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ፤

22 ይሽጳን፥ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥

23 ዓብዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፥

24 ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥

25 ዩፍደያና ፋኑኤል ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

26 ሸምሽራይ፥ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥

27 ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች ነበሩ።

28 እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።

29 የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው በገባዖን የተቀመጠው የገባዖን አባት ይዒኤል፥

30 የበኩር ልጁ ዓብዶን፥ ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥

31 ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር፥

32 ሳምአን የወለደው ሚቅሎት ነበሩ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ።

33 ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ።

34 የዮናታንም ልጅ መሪ-በኣል ነበረ፤ መሪ-በኣልም ሚካን ወለደ።

35 የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።

36 አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።

37 ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁም ረፋያ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል ነበሩ፤

38 ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሽዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን ይባሉ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።

39 የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኩሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት ነበሩ።

40 የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኃያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ ኀምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos