ሮሜ 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆች እንዲሆኑት ተስፋ ያናገረለት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፤ እነዚህ ከሥጋ የተወለዱ ግን የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ማለት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሥጋ ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን የአብርሃም ልጆች የተባሉት የተስፋው ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የሥጋ ልጆች የሆኑት የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን የተስፋው ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ ማለት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሥጋ የተወለዱት የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን ዘር ሆነው የሚቈጠሩት የተስፋው ቃል ልጆች ብቻ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው። |
በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረጀችበት ወራት ዘር ታስገኝ ዘንድ በእምነት ኀይልን አገኘች፤ ተስፋ የሰጣት የታመነ እንደ ሆነ አምናለችና።