ሮሜ 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓለም ባለማወቅ ለከንቱ ነገር ተገዝቶአልና በተስፋ ስለ አስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተዳርጓል፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ ለተስፋ እንዲገዛ ካደረገው ከፈቃዱ የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ ይኸውም በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በተስፋ እንዲገዛ ባደረገው በእርሱ ፈቃድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍጥረት ሁሉ ከንቱ እንዲሆን ተፈርዶበታል፤ ይኸውም በራሱ ፍላጎት ሳይሆን በተስፋ እንዲጠባበቅ ባደረገው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤ |
እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደርሶአል፤ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተመልታለችና፤ እኔም እነሆ፥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
በሚኖሩባት ሰዎች ክፋት ምድሪቱ የምታለቅሰውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ፍጻሜያችንን አያይም ብለዋልና እንስሶችና ወፎችም ጠፍተዋል።
ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ በእርስዋም ከሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፤ ከምድርም ተንቀሳቃሾች ጋር ትጠፋለች፤ የባሕሩም ዓሦች ያልቃሉ።
እንግዲህ ለራሳችን ምን እንሰብስብ? የእንስሳት ጠባቂዎች አለቀሱ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና፥ የበጎች መንጋዎችም ጠፍተዋልና።