Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤ የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣ የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርሷም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር በድካም ይዝላሉ፤ የባሕሩም ዓሦች እንኳ ያልቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህም ምክንያት በምድሪቱ ላይ ድርቅ ይመጣል፤ በእርስዋ የሚኖሩ ሁሉ ይደክማሉ፤ እንስሶች፥ ወፎችና የባሕር ዓሣዎች ሁሉ ያልቃሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርስዋም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር ይደክማሉ፥ የባሕሩም ዓሦች ያልቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 4:3
17 Referencias Cruzadas  

ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ባሕሩንም ይገሥጻታል፥ ያደርቃትማል፥ ወንዞችንም ሁሉ ያደርቃል፣ ባሳንና ቀርሜሎስም ላልተዋል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል።


ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በየ​አ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆ​ናል፤ በየ​መ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባ​ላል፤ ገበ​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ልቅሶ፥ አል​ቃ​ሾ​ቹም ወደ ዋይታ ይጠ​ራሉ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የተ​ነሣ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ችና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ኖሩ ሰዎች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ተራ​ሮ​ችም ይገ​ለ​ባ​በ​ጣሉ፤ ገዳ​ላ​ገ​ደ​ሎ​ችም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ቅጥ​ርም ሁሉ ወደ ምድር ይወ​ድ​ቃል።


በሚ​ኖ​ሩ​ባት ሰዎች ክፋት ምድ​ሪቱ የም​ታ​ለ​ቅ​ሰ​ውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚ​ደ​ር​ቀው እስከ መቼ ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጻ​ሜ​ያ​ች​ንን አያ​ይም ብለ​ዋ​ልና እን​ስ​ሶ​ችና ወፎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋል።


ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ ሸሽ​ተው ነበር።


በውኑ ምድ​ሪቱ ስለ​ዚህ ነገር አት​ና​ወ​ጥ​ምን? በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖር ሁሉ አያ​ለ​ቅ​ስ​ምን? ጦር​ነት እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ እንደ ግብ​ፅም ወንዝ ይሞ​ላል፤ ደግ​ሞም ይወ​ር​ዳል።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”


ምድር አለ​ቀ​ሰች፤ ሊባ​ኖስ አፈረ፤ ሳሮ​ንም እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ገሊ​ላና ቀር​ሜ​ሎስ ታወቁ።


በተ​ራ​ሮቹ ላይ አል​ቅሱ፤ በም​ድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍ​ት​ዋ​ልና፤ የሚ​መ​ላ​ለ​ስም የለ​ምና ሙሾ​ው​ንም አሙሹ፤ የሰ​ማይ ወፍ ድም​ፅ​ንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይ​ሰ​ሙም፤ ደን​ግ​ጠ​ውም ተማ​ር​ከው ሄዱ።


ዝሙ​ታ​ቸው ምድ​ርን ሞል​ት​ዋ​ልና፥ ከመ​ር​ገም ፊት የተ​ነሣ ምድር አል​ቅ​ሳ​ለች፤ የም​ድረ በዳ ማሰ​ሪ​ያው ሁሉ ደር​ቆ​አል፤ ሥራ​ቸ​ውና ድካ​ማ​ቸው ከንቱ ሆነ።


እን​ግ​ዲህ ለራ​ሳ​ችን ምን እን​ሰ​ብ​ስብ? የእ​ን​ስ​ሳት ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቀሱ፤ ማሰ​ማ​ሪያ የላ​ቸ​ው​ምና፥ የበ​ጎች መን​ጋ​ዎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋ​ልና።


እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።


በውኑ ስለ​ዚህ ነገር በመ​ቅ​ሠ​ፍት አል​ጐ​በ​ኝ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios