በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ አልበቃውም፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤያትባሔልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በዓልን አመለከ ሰገደለትም።
ሮሜ 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተገለጠለትስ ምን አለው? “ለጣዖት ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቻለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የሰጠው መልስ ግን ምን ነበር? “ጕልበታቸው ለበኣል ያልተንበረከከውን ሰባት ሺሕ ሰዎች ለራሴ አስቀርቻለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን መለኮታዊ መልስ ምን አለው? “ለበዓል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ብሎ መለሰለት? “ባዓል ለተባለው ጣዖት ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለራሴ አስቀርቻለሁ” ብሎታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ። |
በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ አልበቃውም፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤያትባሔልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በዓልን አመለከ ሰገደለትም።
ኤልያስም፥ “ሁሉን ለሚገዛ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና፤ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ” አለ።
እኔም ከእስራኤል ጕልበታቸውን ለበዓል ያላንበረከኩትን ሁሉ፥ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ።”
እኔም ያላዘዝሁትን፥ ያልተናገርሁትንም፥ ወደ ልቤም ያልገባውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለበዓል ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና፤
እርስዋም እህልንና ወይንን ዘይትንም የሰጠኋት፥ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም። እርስዋ ግን ወርቁንና ብሩን ለጣዖት አደረገች።
ብዔልፌጎርን የተከተለውን ሰው ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ለይቶ አጥፍቶታልና አምላካችሁ እግዚአብሔር በብዔልፌጎር ያደረገውን ዐይኖቻችሁ አይተዋል።