ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ነውና። ንጉሣችንም የእስራኤል ቅዱስ ነውና።
ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።
ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድ ላይም አጥለቀለቁኝ።
የቅርብ ወዳጆቼንና ጓደኞቼን ከእኔ አርቀህ ጨለማ ብቻ ከእኔ ጋር እንዲቀር አደረግህ።
በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።
አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ሐሤትም አድርጉ፤ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ በእርሱ ተመኩ።
በተግሣጽህ ስለ ኀጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ ሰውነቱንም እንደ ሸረሪት አቀለጥኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከንቱ ይታወካሉ።
አቤቱ የኀያላን አምላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እውነትም ይከብብሃል።