መዝሙር 60:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፤ በክንፎችህ ጥላም እጋረዳለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣ ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፥ ተናውጣለችና ቁስልዋን ፈውስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጠላት መሣሪያ ማምለጥ እንዲችሉ፥ የሚፈሩህ አይተው የሚጠነቀቁበትን ምልክት ሰጠሃቸው። |
ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የቀሩትን ይሰበስባል፤ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፤ ዓርማዬንም ወደ ደሴቶች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ታቅፈው ያመጡአቸዋል፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።
በሩቅ ላሉ አሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነሆም፥ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ። መቅሠፍትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ኀይለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመጣል።