መዝሙር 58:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፤ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ አልሰማ ብላ ጆሮዋን እንደ ደፈነች እፉኝት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤ እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ። |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
እነሆ አስማት የማይከለክላቸውን የሚገድሉ እባቦችን እሰድድባችኋለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?