መዝሙር 138:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ጥልቁም ብወርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለውን ዐላማ ይፈጽማል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ለዘላለም ነው። የእጅህንም ሥራ ቸል አትበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ብድራትን ይመልስልኛል፥ አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ለዘለዓለም ነው፥ አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገባኸውን ቃል ኪዳን ትፈጽምልኛለህ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ፍቅርህ ዘለዓለማዊ ነው፤ የእጅህን ሥራ ወደ ፍጻሜ ሳታደርስ አትተወው። |
ባልንጀራውን በስውር የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፤ በዐይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም።
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
እና የእግዚአብሔር ጠላቶቹ ስንሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታረቀን በኋላም በልጁ ሕይወት እንዴት የበለጠ ያድነን!
እርሱ የጀመረላችሁን በጎውን ሥራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ እርሱ እንደሚፈጽምላችሁ አምናለሁ።